ለ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ተቃሚ መረጃ ስለ አ.ሳ.ቴ.ዩ እና አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ በ INNOVATE AASTU የተዘጋጀ

ሰላም፣ ውድ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ማለትም በ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እና አድስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ገብታችሁ ማጥናት የምትፈልጉ ተማሪዎች ፤ ከፈተናው በፊት ከሁለቱ ጊቢዎች ስትመርጡ ይረዳቹ ዘንድ እንዲሁም ጊቢ ከገባችሁ በኋላ ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብኩትን በዚህች አጭር ፁሁፍ ላይ አስፍረያለሁ።

ስለ AASTU የበለጠ መረጃ ይህን አፕ አውርዳቹ መየት ትችላላችሁ:: Download AASTU STUDENTS APP

1. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ

በ አዳማ ከተማ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር በ 1993 ከአዲስአበባ በ 92 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በምትገኘዉ የአዳማ ከተማ የተከፈተ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ከ 20,000 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ አያስተናገደ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ የ አርክቴክቸር እና ሲቪል ኢንጅነሪንግ፣ ሜካኒካል ማቴሪያልስ እና ኬሚካል ኢንጅነሪንግ፣ ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩቲንግ እና አፕላይድ ሳይንስ ኮሌጆች አሉት፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ ከዋናዉ ግቢ ተጨማሪ በ አሰላ ቅርንጫፍ አለዉ፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ በ ስነጥበባት፣ በቢዝነስ እና ማህበራዊ ሳይንስ፣ በቋንቋ፣ በህክምና እና ሌሎች የ ጤና ዘርፎች፣ ኢንጅነሪንግ፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በ ማስተርስ ደረጃ ይሰጣል፡፡ የዶክትሬት ዲግሪ በስነጥበባት፣ በቢዝነስ እና ማህበራዊ ሳይንስ እና ኢንጅነሪንግ ዘርፎች ይሰጣል፡፡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በኋላ የራሱን መግቢያ ፈተና በማዘጋጀት ይቀበላል፡፡

2. አድስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ

አዲስአበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር በ2011 ዓ.ም. በአዲስአበባ ከተማ የተቋቋም ዩኒቨርሲቲ ነዉ፡፡ዩኒቨርሲቲዉ የ አርክቴክቸር እና ሲቪል ኢንጅነሪንግ፣ ባዩሎጂካል እና ኬሚካል ኢንጅነሪንግ፣ ኤሌክትሪካል እና መካኒካል ኢንጅነሪንግ እና አፕላይድ ሳይንስ ኮሌጆች አሉት፡፡ ዩኒቨርሲቲዉ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለዉ ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በኋላ የራሱን መግቢያ ፈተና በማዘጋጀት ነዉ፡፡

የሶፍትዌር እንጂኔሪንግ በሁለቱ ጊቢዎች

በአሁኑ ሰዓት digital skill ይበልጥ ተፈላጊ እየሆነ በመምጣቱ እና ጊዜውም ጋር ተያይዞ ኮምፒውተር ሳይንስና ሶፍትዌር በተማሪዎች ብዙ ፍላጎት የምታይበት የትምህርት አይነት ነው። ለማሳያነትም በዚህ አመት(2013 batch) በAASTU ከሚገኙ የእንጂነሪንግ የአንደኛ አመት ተማሪዎች ውስጥ ከ 900 ተማሪዎች የሶፍትዌር ዲፓርትመንት መግቢያ ፈተና ለመውሰድ 'ተመዝግበዋል'። የአ.ሳ.ቴ.ዩ የሶፍትዌር እንጂኔሪንግ የቅበላ አቅም 200 ተማሪ ሲሆን ኮምፒውተር ሳይንስ አያስተምርም። በአንፃሩ አዳማ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ዲፓርትመንት ሲኖረው ሶፍትዌር እንጂኔሪንግ በተያየዘው አመት ይጀመራል ተብሏል (እስከ አሁን ማስተማር አልጀመረም)።

Applied ሳይንስ በሁለቱ ጊቢዎች

አፕላይድ ሳይንስ ኮሌጅ ትምህርት በሁለቱም ጊቢዎች ከኢንጂነርንግ አንፃር አነስ ያለ የተማሪ ብዛት አለው።
በአድስ አበባ-AASTU የአፕላይድ ድፓርትመንቶች
●Bio Technology
●Industrial Chemistry
●Geology... ናቸው።

በአዳማ - ASTU የአፕላይድ ዲፓርትመንቶች ስር የሚሰጡት
●Applied Biology
●Applied Chemistry
●Applied Geology
●Applied Mathematics
●Applied Physics
Pharmacy ....ናቸው። በጊብዎች የተማሪዎች ብዛትና የቅበላ አቅም ስለምመጣጠን ሁሉም በሚባል ጀረጃ የመረጠው ይሰጠዋል፣ በመጀመሪያው ሴሚስተር ከእንጂነርንግ ወደ አፕላይ መቀየር ይቻላል።

አርክቴክቸራል ሳይንስ በሁለቱ ጊቢዎች

የአድስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የአርክ ዲፓርትመንት የቅበላ አቅም 50 ተማሪ ብቻ ነው። ተማሪዎችንም የምቀበለው 2 የመጊብያ ፈተና በመስጠት (drawing sketch + theory) ነው። በተመሳሳይ ሰዓት አርክ እና ሶፍትዌር መመዝገብ አይቻልም።

ሌሎች እንጂኔሪንግ ዲፓርትመንት በሁለቱ ጊቢዎች

ሌሎች ዲፓርትመንቶች (ኤሌክትሪካል፣ ሲቪል፣ መካኒካል ..ሌሎችም)፤ በሁለቱም ጊቢዎች ከ 3 ሴሚስተር በኋላ (በአዳማ-ASTU ሁለት ሴሚስተር pre-Engineering ተምራችሁ School ትመርጡና ቀጥሎ 1 ሴሚስተር ተጨማሪ ኮርሶችን ወስዳችሁ ከተማራችሁ በኋላ። እንዲሁም በአድስ አበባ-AASTU 2 ሴሚስተር freshman ተምራችሁ 1 ሴሚስተር pre Engineering ተምራችሁ ትመርጣላችሁ። አንዳንድ ዲፓርትመንቱ ላይ እንደየጊቢው የተለያየ የፍላጎት ብዛት ብኖርም የምትፈልጉትን ለመግባት ያን ያህል የተጋነነ ውድድር የለውም!


መልካም የትምህርት ዘመን!

Gemechis Elias

Second year Software Engineering student at AASTU. started programming when he was at highschool, published more than 6 Android Apps on Google PlayStore.